Saturday, 26 December 2015

Historic

እነዚህ ሰዎች እስከመቼ ታሪክን እያግበሰበሱ ይኖራሉ?
የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ስለ ኣጼ ቴዎድሮስ ትግራዋይነት በሚተነትነው ጽሁፌ ላይ <<ኣጼ ቴዎድሮስ ኣባት የሌላቸው ሆኖ ነው በቋራ ተወላጇ እናታቸው <<ጎንደሬው የኮሶ ሻጭ ልጅ ካሳ>> ብለው የሚጠሩት?>> ስል ረጅም ጽሁፍ ማቅረቤንና ወደ460 ሰዎች ሼር ማድረጋቸውንም ኣስታውሳለሁ። በዚህም በጣም ገረመኝ፤ምክንያቱም ለእናት ሃገር ኢትዮጵያ በሰሩት ስራ ኣጼ ቴዎድሮስንና ኣጼ ሚኒሊክን ማወዳደር እብደት ነው።ኣጼ ዮሃንስንና ኣጼ ቴዎድሮስን ማነጻጸር ደግሞ ቅሌት ነው።
ኣጼ ቴዎድሮስ ከጎንደርና ከደቡብ ወሎ በቀር ኤርትራንና ጅማን ጨምሮ ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍል ልክ እንደ ኣጼ ዮሃንስን ኣላስተዳደሩም፤ይህን ያደረጉ ኣጼ ዮሃንስን ብቻ ናቸውና።ሌላው ኣጼ ቴዎድሮስ 4 ግዜ ከመሳፍንት ጦርነት ገጥመው 4ቱም ድል ሲያደርጉ 1 ግዜ ከእንግሊዝ ገጥመው ተስፋ ቆርጠው በጠጧት የሽጉጥ ጥይት ለህልፈተ ሂወታቸው ተዳርገዋል።
ኣጼ ዮሃንስ ወደ 6 የሚጠጕ የሃገር ውስጥ ጦርነቶች ገጥመው 6ቱም ድል ሲያደርጉ ወደ 8 የሚጠጕ ከውጭ ወራሪዎች ጦርነቶች ገጥመው 7ቱም ድል ኣድርገው ከድርቡሾች ያደረጉት የመጨረሻውን ጦርነት በኣወዛጋቢ ሁኔታ መተማ ዮሃንስ ላይ ለህልፈታቸው ተዳርገዋል።
ይሁን እንጂ በወሎ፤በባሕረነጋሽ(ኤርትራ)፤በሸዋ፤በጎጃምና በጅማ የየኣከባቢው ነገስታትን ስለሾሙ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገስት ኣጼ ዮሃንስ ብቻ ናቸው። ሌሎቹ ግን ነገስታትን ስላልሾሙ የኢትዮጵያ ንጉሶች እንጂ ንጉሰ ነገስት የሚለውን መዓረግ ኣግባብ ኣይደለም፤መስተካከል ኣለበት።
ኣጼ ሚኒሊክ ከውጭ ወራሪዎች ጋር ምንም ጦርነት ሳያደርጉ ይልቁንም የኦሮሞና የትግራይ(ኤርትራውያን) ጡትና ብልት በመቁረጥ ስልጣናቸውን ኣጠናክረዋል።ከወላይታው ንጉስ ካዎ ጦና ጋር ያደረጉት የዓፋር ቀልድ ጦርነት ተብላ ከጀብዱ ከተቆጠረችም ያችኑ ብቻ!!! ኣለበለዚያ ሚኒሊክ በኢትዮጵያ የጣልያን ኣምባሳደር የሚለውን የባንዳ ስም ቢያንሳቸው እንጂ ኣይበዛባቸውም።
ስለ ዓድዋ ጦርነት ግን ኣጼ ሚኒሊክን ፈጽሞ እንደማይመለከታቸው <<Central Museum of the Italian Great Patriotic War of 1941-1945>> ከተሰኘው የጣልያን ሙዝየም የተገኘውን ዶክመንት በመጥቀስ
<<ጉዳይ ናይ ዓድዋ እንተኾነ ፡ ዓድዋ ሰሪቶም ዝደኮኑ ኣብሓጎታትና እዮም ፡ጅግንነት ዓድዋ እንተኾነ’ውን ጅግንነት ኣብ ዓድዋ ዝፈጸሙ ብኣብሓጎታትና ኮይኖም ኣጸይምነልክ ኣብ ኲናት ናይ ዓድዋ ዝመስከሮ ሓቂ እንተኾይኑ ፡ ከሺ ኣማራ ኣንድ ኣበራ ` ኢሉዎ እዩ ፡ >> ሲል ( መጽሓፍ ንግስነት ምድረ ባሕሪ ( ኤርትራ ) ብኣቶ ይስሓቕ ዮሴፍ ) ጽፏል።
ኣሁንም የሚገርመኝና የሚያሳዝነኝ ነገር ልሂቃነ ሸዋ የኣጼ ቴዎድሮስ ትግራዋይነት ደብቀው የኣማራ ማንነት ለመስጠት ሲባል <<ጎንደሬው የኮሶ ሻጭ ልጅ ካሳ>> በማለት በየፊልሙ፤በየ ድሪቶ ድርሰቶቻቸው ፤በየ ቲያትሩ፤በየ ሰርግ ቤት ቀረርቶና ሽለላው ሲጽፉ ኣልበቃ ብሏቸው፤ኣሁን ደግሞ ስለ ልጃቸው ልኡል ኣለማየሁ ቴዎድሮስ እናት የሌለው ይመስል<<የቋራው ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል ዓለምአየሁ አስከፊ ስደቱና ሞቱ>> እና ወዘተ መጽሃፎች ሲጻፉ እናያለን።
ጥያቄ ለልሂቃነ ሸዋ ኣለኝ፦
ኣጼ ቴዎድሮስ ኣባት የላቸውም ? ለምን እንደ ዲቃላ በእናታቸው ትጠሯቸዋላችሁ?
ልዑል ዓለምአየሁ እናት የለውም? የእናቱን ማንነት መደበቅ ለምን ኣስፈለገ?
የዚያ ቤተሰብ አባት አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፤ እናት እቴጌ ጥሩ ወርቅ፤ ልጅ ደግሞ ልዑል ዓለማየሁ ካሣ።
ለማስታወስ ያክል የኣጼ ቴዎድሮስ ኣያት ደጃዝማች ወ/ጀወርግስ የወጀራት 20 ዓዲ ባላባት መሆናቸውንና ደጃዝማችነታቸውም በ18ኛው መክዘ ኣጋማሽ የእንደርታ ታዋቂ ባላባት በመሆናቸው ያገኙት መዓረግ ነው።
ደጃዝማች ወ/ጀወርግስ የእንደርታ ታዋቂ ባላባት ሳሉ ከተንቤን ሚስት ኣግብተው ደጃዝማች ኃይሉ ወ/ጀወርግስ ወልደዋል። ደጃዝማች ኃይሉ ደግሞ ቴዎድሮስን በ1816 ዓም ቋራ ላይ በሽሽት ሳሉ ወልደዋል።
ደጃዝማች ኃይሉ ከነ ደጃች ምርጫ ኣብርሃ ወገን ሰው ገድለው ከተንቤን ወደቋራ እንደሸሹ የዛሬ 2ዓመት በሰፊው ኣትቻለሁ።
ዛሬ ደግሞ ስለልጃችው ልኡል ኣለማየሁ እናት ማለትም ስለ ኣጼ ቴዎድሮስ ባለቤት ማንነት እንዲሁ እስከዛሬ ተሸፋፍኖ ላይነገር ዝምምም ተብሏል።
የኣጼ ቴዎድሮስ ባለቤት እቴጌ ጥሩወርቅ ይባላሉ። ትውልዳቸውም ከትግራይ ዓጋመ ኣውራጃ ሲሆን የስባጋድስ ዓጋመ የልጅ ልጅ ናቸው።
(የራስ ወልደስላሴና እቴጌ ጥሩወርቅ የሂይወት ታሪክ ጨለቖት ስላሴ ቤ/ክ ማንም ሰው በኣካል ሂዶ ማየት ይችላል)
አጤ ቴውድሮስ በመቅደላ ሲወድቁ ከባለቤታቸው እቴጌ ጥሩወርቅ የሚወለደው ልዑል አለማየሁ እድሜው 8ዓመት ብቻ ነበር፡፡ልዑል አለማየሁም ከእናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ ጋር በእንግሊዞች እጅ ወደቀ፡፡ጄኔራል ናፒር ከእቴጌ ጥሩወርቅ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት አጤ ቴውድሮስን በቅርበት ያውቃቸው ለነበረው እና አማርኛን አቀላጥፎ ለሚናገረው ካፒቴን ጄ.ሲ. ስፒዲ ተሰጠ፡፡
እነ ናፒር ልዑል አለማየሁ ከእናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ፤ከመምህሩ አለቃ ዘራኣት፤የእናቱ አጃቢ ኣለቃ ገብረመድህን ጋር ሆኖ ከሃገሩ እንዲወጣ አደረጉ፡፡በመንገድ ላይ እናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡በሞቱ ጊዜም በትግራይ ክፍለሃገር በእንደርታ ኣውራጃ በሚገኘው በዘመነ መሳፍንት የትግራይ ግዥ ከነበሩት ራስ ወልደስላሴ በተቀበሩበት በጨለቖት ደብረ ገዳም ስላሴ ቤተክርስትያን ተቀበሩ።
(አጤ ቴዎድሮስ መጽሃፍ በጳውሎስ ኞኞ)
ስለዚህ የዚያ ቤተሰብ አባት አፄ ቴዎድሮስ ፤ እናት እቴጌ ጥሩ ወርቅ እና ልጅ ደግሞ ልዑል ዓለማየሁ ካሣ ሁሉም ተጋሩ ናቸው።
ከምንሊክ ሌላ ንጉስ የላችሁም፤ፍጹም ሊኖራችሁም ኣይችልም።
እናም እስከመቼ ታሪክን እያግበሰበሳቹህ ትኖራላቹ?
በኢትዮጵያ 3 የኣማራ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ኣሉ እነሱም፦
የሸዋ ልሂቃን፤የኣማራ ክልል ባ/ቱ/ ቢሮ እና ማህበረ ቅርሱሳን ሲሆኑ፤
በትግራይ ግን የህወሓት ጽ/ቤት ካልሆነ በቀር እስካሁን የባህልና ቱሪዝም የሚባል ቢሮ የለም።

No comments:

Post a Comment